ለዳይሬክተሮች ቦርድ አባልነት እጩዎችን ለመጠቆም የወጣ ማስታወቂያ

ለዳይሬክተሮች ቦርድ አባልነት እጩዎችን ለመጠቆምየወጣ ማስታወቂያ

በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ መመርያ ቁጥር SBB 71/2019 አንቀጽ 6.1.4. መሰረት በባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባኤ የተሰየመው የባንካችን አስመራጭ ኮሚቴ ስራውን የጀመረ በመሆኑ፣ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ህጋዊ መስፈርቶች የሚያሟሉ የእጩ ዳይሬክተሮች ጥቆማን ከባንኩ ባለአክሲዮኖች ከግንቦት 24 ቀን 2012 እስከ ነሐሴ 25 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ ይቀበላል፡፡

ለቦርድ አባልነት በዕጩነት ለመጠቆም የሚያበቁ መስፈርቶች፡-

 1. የባንኩ ባለአክሲዮን የሆነ/የሆነች፣ ቢመረጥ/ብትመረጥ ለመሥራት ፈቃደኛ የሆነ/ች እና እድሜው/ዋ 30 ዓመትና

ከዚያ በላይ የሆነ፤

 1. የመጀመሪያ ዲግሪና ከዚያ በላይ ወይም ተመጣጣኝ የትምህርት ደረጃ ከታወቀ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ያለው/ያላት፤ሆኖ ተጠቋሚዎች የባንኪንግ፣ ፋይናንስ፣ አካውንቲንግ፣ማኔጅመንት፣ ኢኮኖሚክስ፣ ህግ፣ ንግድ አስተዳደር፣ ኦዲት፣ አይ.ቲ እና ኢንቨስትመንት አመራር ባለሙያዎች ቢሆኑ ይመረጣል፤
 2. በቢዝነስ ማኔጅመንት በተለይ በባንኪንግ ቢዝነስ በቂ ልምድ ያለው/ያላት እና/ወይም በዳይሬክተሮች ቦርድ አባልነት ከተመረጠ/ች በኋላ ከባንክ ሥራ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ስልጠናዎች ለመውሰድ ፈቃደኛ የሆነ/ች፤
 3. የአስመራጭ ኮሚቴ አባል ያልሆነ/ች፤ እንዲሁም የኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክም ሆነ የሌላ ባንክ ሰራተኛ እንዲሁም የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል ያልሆነ/ች፤
 4. በኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ በዳይሬክተሮች ቦርድ አባልነት ከስድስት ተከታታይ ዓመታት በታች የሰራ/የሰራች፣ ወይም ለተከታታይ ስድስት ወይም ዘጠኝ ዓመታት በቦርድ አባልነት በማገልግል የአገልግሎት ዘመኑን/ኗን ካጠናቀቀ/ች በኋላ ስድስት ተከታታይ ዓመታት የሞላው/የሞላት፤
 5. የህግ ሰውነት ያለው ድርጅት በእጩነት ሊጠቆም ይችላል፤ሆኖም በጥቆማው ወቅት ድርጅቱን የሚወክልና እዚህ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟላ/የሚታሟላ የተፈጥሮ ሰው ማሳወቅ አለበት፤
 6. መልካም ስነምግባርና ማህበራዊ ተቀባይነት ያለው/ያላት፣ እና በወንጀል ተከስሶ/ተከሳ ያልተቀጣ/ያልተቀጣች፤
 7. የፋይናንሺያል ጤናማነት መስፈርት የሚያVላ/የሚታሟላ፣ ማለትም በኪሳራ ላይ ያልሆነ/ች፣ የታክስና የባንክ ግዴታዎቹን/ቿን የተወጣ/ች፤
 8. መስፈርቱን የሚያሟሉ ሴት ዕጩዎችን መጠቆም ይበረታታል፤
 9. ከሚጠቆሙ  እጩዎች 1/3ኛዎቹ የሚጠቆሙት ከባንኩ ጠቅላላ የተፈረመ ካፒታል 2 ከመቶ በታች ባላቸው (ተጽዕኖ ፈጣሪ ባልሆኑ) ባለአክሲዮኖች ብቻ ሲሆን ቀሪ 2/3ኛዎቹ በሁሉም ባለ አክስዮኖች ይጠቆማሉ፡፡

በዚሁ መሠረት ከላይ በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ የባንኩ ባለአክሲዮን የሆናችሁ ከላይ የተዘረዘሩ መስፈርቶችን የሚያሟሉ የዳይሬክተሮች ቦርድ እጩዎችን ለመጠቆም የተዘጋጀውን ቅጽ ከባንኩ ዋና መ/ቤት 2ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 201-A ወይም በአቅራቢያዎ ካሉ የባንኩ ቅርንጫፍ  በመውሰድ ወይም ከባንኩ ድህረ-ገፅ (www.orointbank.com )  በማውረድ ለዳይሬክተሮች ቦርድ አስመራጭ ኮሚቴ በሚከተሉት መንገዶች ጥቆማ እንድታቀርቡ ተጋብዛችኋል፡፡

 1. ቦሌ አፍሪካ ጎዳና ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ ዋና መ/ቤት ህንጻ፤ 2ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥቆማና አስመራጭ ኮሚቴ ቢሮ ቁጥር 201-A ወይም በአቅራቢያዎ ባሉ የባንኩ ቅርንጫፍ በአካል በማስረከብ፤ ወይም
 2. በፖስታ ሳጥን ቁጥር 27530/1000 አዲስ አበባ፣ በአደራ ደብዳቤ በመላክ፤ወይም
 3. በአስመራጭ ኮሚቴው ኢሜይል አድራሻ፡ oibelectnom1@gmail.com ላይ በመላክ ጥቆማውን መስጠት ይቻላል፡፡

ማሳሰቢያ፤

 1. ከላይ በተዘረዘሩት ሶስቱም አማራጮች የሚላክ የጥቆማ ቅፅ፣ በትክክል ተሞልቶ በጠቋሚው ባለአክሰዮን መፈረም ይኖርበታል፤ ጠቋሚው ባለአክስዮን ድርጅት ከሆነ፣ በሁሉም የጥቆማው ቅጽ ገፆች ላይ የድርጅቱ ማህተም መመታት አለበት፡፡
 2. ጠቋሚ ባለአክስዮኖች የሞሉትን የጥቆማ ቅፆች፣ በባንኩ ዋና መ/ቤትና ቅርንጫፍ በአካል የሚያስረክቡ ከሆነ፣ እራሳቸው በአካል በመገኘት እና ማንነታቸውን የሚገልጽ መታወቂያ በማሳየት ወይም በህጋዊ ወኪላቸው አማካይነት ማስረከብ አለባቸው፡፡
 3. ከላይ በተ.ቁ 1 እና 2 በተገለፁት ሁኔታዎች ያልተላኩ የጥቆማ ቅፆች ተቀባይነት አይኖራቸውም፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡ 011-558-54-12 መደወል ይችላሉ፡፡

           የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥቆማና አስመራጭ ኮሚቴ    

                              የህዝብ ባንክ!

Leave a Reply

Your email address will not be published.