ተጨማሪ ጥቅም የሚያስገኝ የቁጠባ ሂሳብ

ይህ የቁጠባ ዓይነት ለሠራተኞች(ደሞዝተኞች) የተዘጋጀ ሲሆን የተወሰነ የገንዘብ መጠን ከቆጠቡ በኃላ ለቤት ወይም ለመኪና መግዣ ብድር የሚያገኙበት አገልግሎት ነዉ፡፡

የአገልግሎቱ መሠረታዊ ባህሪያት

  • የሥራ ካፒታላቸዉን ለማሳደግ፣ ቢዝነስ ለመጀመር አልያም ለማስፋፋት ሲቆጥቡ ለነበሩ ደንበኞች የተመቻቸ የብድር አገልግሎት ነዉ፤
  • ተቀማጭ ገንዘቡ ባንኩ ያስቀመጠዉ የጊዜ ገደብ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ወጭ ማድረግ አይቻልም፤
  • በግንኙነት እና በቢዝነሱ ሁኔታ ላይ ተመርኩዞ የብድር ወለድ ምጣኔዉ ዝቅ ልል ይችላል፡፡
  • በኮንትራት ዉሉ መሠረት ብሩ የሚቀመጥበት ጊዜ እንደተጠናቀቀ አስቀማጩ ዋናዉንና ወለዱን የሚችል ሲሆን በቀላል ማስያዣ እና በዝቅተኛ ወለድ መበደር ይችላል፤
  • የፕሮግራሙ ጊዜ ሲጠናቀቅ ደንበኛዉ የቆጠበዉን ገንዘብ ማዉጣት ፣ ዉሉን ማደስ አልያም ወደ በጊዜ የተገደበ ተቀማጭ ሂሳብ መቀየር ይችላል፡፡