ኢንቨስትመንት ሶሉዩሽን ሂሳብ

ኢንቨስትመንት ሶሉዩሽን ሂሳብ/የእቅድ ቁጠባ ሂሳብ ማለት  ኢንቨስትመንት ቁጠባ  የቆጣቢዎችን ዓላማ ከግብ ለማድረስ የሚከፈት ሲሆን፤ኢንቨስትመንት ሶሉዩሽን ሂሳብ ቁጠባ የሚከፈተዉ  ለተለየ ፈይዳ እና ለተወሰነ ጊዜ ነዉ፡፡

የዚህ ሂሳብ ዋና ዋና መለያዎቹ

  • ይህ ሂሳብ መከፈት ያለበት ለበዓላት፤ለእረፍት ጊዜ፤ ወይም ለተለየ አላማ ቁጠባ ሲሆን የሂሳቡ ባለቤት ይህን ሂሳብ በመክፈት እነኚህን የተለዩ ኩነቶችን ማለትም ለፕሮጀከት፤ለእረፍት፤ለጉዞ፤ለሰርግ ወይም ለምርቃት እቅዶችን ለማሳካት የሚከፍተዉ ሂሳብ ነዉ፡፡
  • በአንድ ሰዉ ወይም በጋራ የሚንቀሳቀስ ሂሳብ ነዉ፡፡
  • የመጀመሪያ ቁጠባ ሲከፈት ባንኩ የማጣራት(የመለየት) ስራን መስራት ይኖርበታል፤
  • መደበኛዉ ቁጠባ በቀን፤በሳምንት፤ ወይም በወር መሰረት ሊሆን ይችላል፡፡
  • ከተቀመጠዉ የጊዜ ገደብ ዉጪ ደንበኛዉ ከሂሳቡ ወጪ ማድረግ አይችልም፡፡
  • ቀነ ገደቡ በደረሰ ጊዜ ደንበኛዉ ሙሉ ገንዘቡን ከነወለዱ ማዉሰድ ይችላል፡፡
  • ደንበኛዉ ከተቀመጠዉ የጊዜ ገደብ በፊት ገንዘቡን ማዉጣት ከፈለገ በተስማማዉ መሰረት ወይም በቅጣት ማለትም ገንዘብ ወጪ በሆነበት ጊዜ ሁሉ ወለድ አይኖረዉም፡፡
  • ከመደበኛዉ ቁጠባ ሂሳብ የተለየ ወለድ ምጣኔ ሊኖረዉ ይችላል፡፡