ዝግ ሂሳብ

ይህ አገልግሎት የቼክ ክፍያ ሶሉሽን መዋቅር/አሰራር (CPSS) ተብሎም ተሰይሟል፡፡ ከደንበኛዉ የቁጠባ ሂሳብ ጋር የተጣመረም በመሆኑ በተንቀሳቃሽ ሂሳብ ላይ ያለዉ መጠን በቼክ ከተገለጸዉ መጠን ቢያንስም ቼኩ ተመላሽ አይደረግም፡፡

የአገልግሎቱ መሰረታዊ ባህሪያት

  • የዚህ ሂሳብ የገንዘብ ፀባይ ደንበኛዉ በቂ ሂሳብ ሳይኖር ለተጻፈ ቼክ ተጠያቂ ከመሆን እና ሂሳቡን ከማዘጋት ቼኩን መክፈል ያስችላቸዋል፡፡
  • የሂሳቡ ባለቤት የቁጠባ ሂሳቡን እና ተንቀሳቃሽ ሂሳቡን ለማጣመር ለባንኩ መፍቀድ/መስማማት አለበት፡፡
  • የተንቀሳቃሽ ሂሳቡ ድርሻ/ክፍል ወለድ የሌለዉ/የማያስገኝ ሲሆን የቁጠባ ሂሳቡ ድርሻ/ክፍል መደበኛ የወለድ ምጣኔ ያስገኛል፡፡
  • 5,000,000 እና ከዛ በላይ ያለዉ የቁጠባ ሂሳብ ያላቸዉ ለዚህ ልዩ መብት/ጥቅም ተመራጭ ናቸዉ፡፡ (የ5,000,000 ብር ገደቡ በዋናነት በሌሎች ባንኮች የተቀመጠ ሲሆን የኛ ባንክ ካስፈለገ/እንደየአስፈላጊነቱ ሌላ መጠን ሊጠይቅ ይችላል፡፡)
  • ዝቅተኛ የጠቀማጭ መጠን እሰከሚቀር ድረስ በዚህ አገልግሎት ከቁጠባ ሂሳብ የወጪ መጠን ያልተገደበ ነዉ፡፡
  • በተንቀሳቃሽ ሂሳብ ላይ አነስተኛ ቀሪ ሂሳብ ሲኖር ደንበኛዉ ወዲያዉ ለቼክ ክፍያ የቁጠባ ሂሳቡን መጠቀም/መገልገል ይችላል፡፡
  • የተንቀሳቃሽ ሂሳብ ቼክ ክፍያ ፕሮቴክሽን አሰራር ከቁጠባ ሂሳብ ወጪ ሲደረግ ለደንበኛዉ ወዲያዉ አጭር የጽሁፍ መልዕክት ይደርሰዋል፡፡