የፕሮቪደንት ፈንድ ሶሊዩሽን ሂሳብ

የፕሮቪዴንት ፈንድ ሶሊዩሽን ሂሳብ የተቀማጭ ገንዘብ ቁጠባ ሲሆን ፕሮቪዴንት ፈንድን ለማስተዳደር የሚከፈት ነዉ፡፡ ይህ የግል ድርጅቶች ለሠራተኞቻቸዉ የሚከፍቱት ሂሳብ ነዉ፡፡

የአገልግሎቱ መሠረታዊ ባህርያት

  • ሂሳቡ በዜሮ ሂሳብ በሰራተኛዉ ስም ሊከፈት ይችላል፤
  • ደንበኞች ከመደበኛ ቁጠባ የበለጠ ወለድ ያገኙበታል፤
  • ባንኩ ለተለያዩ ዕቃዎች፣ ቤት፣ መኪና እና ሌሎች ቋሚ ንብረት መግዣ የተጠራቀመዉን የፕሮቪዴንት ፈንድ መጠን ያለዉ ለባለሂሳቡ ማበደር ይችላል፡፡
  • ባንኩ ያለምንም ክፍያ በየወሩ የሂሳብ እንቅስቃሴ መግለጫ ሊሰጥ ይችላል፡፡