የቁጠባ ሳጥን ሂሳብ

ይህ አገልግሎት አንድ ሰው ገቢው አነስተኛ በመሆኑ ምክንያት ሊያጋጥመው የሚችለውን ምልልስ ለመቀነስ በሳንቲም ደረጃ በባንኩ ሳጥን ውስጥ በማጠራቀም ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ወደ ባንኩ ቅርንጫፍ በመሄድ መቆጠብ የሚያስችል ነው፡፡ ዋናው ዓላማም ሰዎች የመቆጠብ በህላቸውን እንዲያጠናክሩ ለማስቻልም ጭምር ነው፡፡

  • የደንበኛዉ ሥራ ምንም ይሁን ወደ ባንክ መምጣት ሳያስፈልግ በየቀኑ ሸርፍራፊ ሳንቲሞችን ማጠራቀም ይችላል፤
  • ይህ አገልግሎት በየሳምንቱ፣ በየሁለት ሳምንት፤ በየቀኑ አልያም ደንበኛዉ በፈለገዉ ጊዜ ይሰጣል፤
  • የቁጠባ ሳጥኑ የ24 ሰዓት ገንዘብ የማጠራቀም አገልገሎት የሚሰጥ ሲሆን ወጪ ማድረግ የሚቻለዉ ግን ባለሂሳቡ ወደ ቅርንጫፍ ሲሄድ ብቻ ነዉ፤
  • ተቀማጭ ገንዘቡን ለመጠቀም ቁልፍ ወሳኝ ነገር ነዉ፤