በቼክ የሚንቀሳቀስ የቁጠባ ሂሳብ

በቼክ የሚንቀሳቀስ የቁጠባ ሂሳብ ነዉ፡፡ ሌሎች ባንኮች ዘንድ ቅይጥ የተቀማጭ ሂሳብ በመባል ይታወቃል፡፡

የአገልግሎቱ መሠረታዊ ባህርያት

  • ወለድ የሚታሰብበት በቼክ የሚንቀሳቀስ የተቀማጭ ሂሳብ ነዉ፤
  • ደንበኞች ወለድ እየታሰበላቸዉ ገንዘባቸዉን በቼክ ማንቀሳቀስ ይችላሉ፤
  • ሂሳቡን ለመክፍትና ለማንቀሳቀስ የተወሰነ ተቀማጭ ገንዘብ መኖር አለበት;
  • ወለድ የሚሰላዉ በየሩብ ዓመት ይሆናል
  • ሂሳቡ ላይ ያለዉ የገንዘብ መጠን ከሚፈለገዉ አነስተኛ የገንዘብ መጠን በታች ሲሆን ቅጣት ይኖራል፤
  • ለባለሂሳቡ አጭር የሂሳብ እንቅስቃሴ መግለጫ በየወሩ ይሰጣል፤
  • ለባለሂሳቡ ደብተር አይሰጥም፡፡