ሐዩ የትምህርት የቁጠባ ሂሳብ

ተማሪዎች የከፍተኛ ትምህርት ለመማር ወይም የወጪ መጋራት(cost sharing) ለመክፈል በዚህ ልዩ የቁጠባ ሂሳብ ከቆጠቡት ገንዘብ በብድር መልክ በመወሰድ ተጠቃሚ የሚሆኑበት ነው፡፡ ለዚህ የቁጠባ ሂሳብ ወለድ የሚታሰበዉ በመደበኛዉ የቁጠባ ሂሳብ መሰረት ነዉ።

ሂሳቡን የሚከፍት ደንበኛ ቋሚ ገቢ ሊኖረዉ ይገባል፡፡ የትምህርት ብድር የሚሰጠው በባንኩ የብድር ፖሊሲ መሰረት ሲሆን አስፈላጊዉ የብድር ዋሰትና(collateral) መቅረብ ይኖርበታል፡፡

  • ለከፍተኛ ትምህርት የብድር አገልግሎት ሲጠየቅ ባንኩ የትምህርት ክፍያዉን ይፈጽማል፤
  • የብድር አገልገሎት ለማግኘት ሂሳቡ በትንሹ አንድ ዓመት መቆየት አለበት፤
  • ሂሳቡ በቁጠባ ደብተር እና/ወይም በኤ.ቲ.ኤም ካርድ ይንቀሳቀሳል፤
  • ሂሳቡ መደበኛ ወለድ የሚታሰብበት ነዉ፤
  • ይህንን ሂሳብ የሚከፍት ሰዉ ቋሚ ገቢ ሊኖረዉ ይገባል፤
  • ሁለተኛ ድግሪ ወይም ፒ.ኤች.ዲግሪ መማር የሚፈልጉ ተማሪዎች ብድር ማግኘት ይችላል፤
  • ለሁለተኛ ድግሪ ወይም ፒ.ኤች.ዲግሪ ብድር እንዲሁም የወጪ መጋራት ክፍያ አገልገሎት ያገኙበታል፤
  • ብድር የሚሰጠዉ በብድር ፖሊሲ መሠረት ተቀባይነት ያለዉ የብድር ማስያዣ (collateral) እና የሚፈለገዉ ተቀማጭ ገንዘብ መጠን ሲኖር ነዉ፤
  • ባለሂሳቡ ለከፍተኛ ትምህርትም ሆነ የወጪ መጋራት ክፍያ ብድር አገልግሎት ለማግኘት የማያስፈልገዉን የተቀማጭ ገንዘብ መጠን እና ሰነዶችን ሲያቀርብ ነዉ፡፡