ሀንዱራ፤ የልጆች የቁጠባ ሂሳብ

ይህ ልዩ የቁጠባ ሂሳብ ወላጆች ወይም አሳዳጊዎች ከ18 ዓመት በታች ለሆኑ ልጆቻቸዉ የሚከፍቱት ሲሆን ልጆች ለወደፊት ትምህርታቸዉንም ሆነ ኑሮአቸዉን የሚመሩበት ልዩ ጥቅም የሚያስገኝ ነዉ፡፡

የአገልግሎቱ መሠረታዊ ባህርያት

  • ሂሳቡን የህፃኑ ወላጆች/አሳዳጊዎች በጋራ ወይም በተናጠል ሊከፍቱ ይችላሉ።
  • የህፃኑ ስም ከወላጆች/አሳዳጊዎች ስም ቀጥሎ መጻፍ አለበት።
  • ይህ የቁጠባ ሂሳብ ሕፃኑ ዕድሜዉ እስኪደርስ የሚንቀሳቀሰዉ በወላጆች ወይም አሳዳጊዎች ነዉ፤
  • ልጁ ሂሳቡን ለማንቀሳቀስ ዕድሜ ላይ እስኪደርስ በቁጠባ ደብተር ይንቀሳቀሳል፤
  • ለዚህ ቁጠባ ሂሳብ ማንኛዉም የክፍያ ካርድ አይሰራለትም፤
  • ሂሳቡ ሲከፈት ያለምንም ክፍያ ሊሆን የሚችል ሲሆን በአንድ ወር ጊዜ ዉስጥ ቁጠባ መጀመር አለበት፡፡
  • በማንኛዉም ጊዜ የፈለጉትን መጠን ገንዘብ ማዉጣት ይችላሉ።
  • ባለሂሳቡ ልጅ 18 ዓመት ሲሞላዉ ክፍያ መቀበል ይችላል፤ ሂሳቡም ወደ መደበኛ የቁጠባ ሂሳብ ይቀየራል።
  • ከ18 ዓመት በኃላ ልጁ ያለ ወላጆች/አሳዳጊዎች እርዳታ ሂሳቡን የማንቀሳቀስ መብት አለዉ፡፡