በጋራ (በሽርክና ላይ የተመሰረተ የፋይናንሲንግ አገልግሎት)

ሙሸራካ የፋይናንሲንግ አገልግሎት (ሽርክና)

በባንኩና በደንበኛው መካከል በቅድሚያ በሚፈጸም የውል ስምምነት መሰረት ሁለቱም ወገኖች በሚያዋጡት የካፒታል ድርሻ በሽርክና የሚሰራ ኢንቨስትመንት ነው፡፡

የሙሸራካ ልዩ ባህሪያትና ጥቅሞቹ፡-

  • በሸሪዓው መርህ በተፈቀዱ የስራ መስኮች ብቻ ይሰማራል፤
  • ባንኩና ደንበኛው የሚያገኙትን ትርፍ በቅድሚያ በተፈረመው ውል በተጠቀሰው የትርፍ ክፍፍል የመቶኛ ስሌት መሰረት የሚከፋፈሉ ይሆናል፤
  • በዚህ የሽርክና ስራ ባንኩም ሆነ ደንበኛው የጋራ ድርጅታቸው ለሚያከናውናቸው ተግባራት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የመሳተፍና የመወሰን መብት ይኖራቸዋል፤
  • ባንኩ ዘለቄታ ያለው ሽርክና አይኖረውም፤ የባለቤትነት ድርሻውን ለሸሪኩ እየሸጠ ይሄዳል፤
  • ቀልጣፋና ግልጽ የሆነ የምክር አገልግሎት በፕሮፌሽናል ባለሞያዎች ከባንኩ ያገኛሉ፤
  • ኢንቨስትመንቱ የደረሰበትን ደረጃ እና ሁኔታ በተለያዩ ወቅቶች ማየት እና መገምገም ይቻላል፡፡

ሙዳረባ የፋይናንስ አገልግሎት

በባንኩና በደንበኛው መካከል በቅድሚያ በሚፈፀም የውል ስምምነት መሰረት ባንኩ በገንዘቡ እንዲሁም ደንበኛው በዕውቀቱ ወይም በሙያው ለሚሰሩት የሽርክና ሥራ የሚቀርብ የኢንቨሰትመንት ፋይናንስ አገልግሎት ነዉ፡፡

የሙደራባ ልዩ ባህሪያትና ጥቅሞቹ፡-

  • በሸሪዓው መርህ በተፈቀዱ የስራ መስኮች ብቻ ይሰማራል፡፡
  • ባንኩና ደንበኛው የሚያገኙትን ትርፍ በቅድሚያ በተፈረመ ውል በተጠቀሰው የትርፍ ክፍፍል የመቶኛ ስሌት መሰረት ይከፋፈላሉ፡፡
  • ኪሳራ ሲደርስ ገንዘብ ባዋጣው ወገን ብቻ የሚሸፈን ይሆናል፡፡
  • ቀልጣፋና ግልጽ የሆነ የምክር አገልግሎት በፕሮፌሽናል ባለሞያዎች ከባንኩ ያገኛሉ፡፡
  • የኢንቨስትመንቱን ደረጃ እና ሁኔታ በተለያዩ ወቅቶች ማየት እና መገምገም ይቻላል፡፡