ኦኢባ እና የኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽን ስምምነት ተፈራረሙ

ኦኢባ እና የኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽን ስምምነት ተፈራረሙ

 

ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ እና የኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽን በጋራ ለመሥራት ስምምነት ተፈራረሙ፡፡ የባንኩ ም/ፕሬዝዳንት አቶ ወልዴ ቡልቶ እና የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ወ/ሮ ለሊሴ ዱጋ ሌሎች የሁለቱም ተቋማት የስራ አመራር በተገኙበት ስምምነቱን ተፈራርመዋል፡፡
በዚህም መሠረት ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ የቱሪዝም ዘርፉን ለመደገፍ፣ ኮሚሽኑ ለ500 ሺህ ወጣቶች የሥራ ዕድል ለመፍጠር የያዘዉን ዕቅድ ለመደገፍ፣ የኢንተርፕሩነርሺፕ ስልጠናዎችን ለመስጠት እንዲሁም አጠቃላይ የባንክ አገልግሎትን በመስጠት ጠንካራ የስራ ግንኙነት ለመፍጠር ተስማምተዋል፡፡

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.