ብድር እና ቅድመክፍያዎች

ባንካችን የተለያዩ ፕሮጀክቶችን እና የንግድ ሥራዎችን ፋይናንስ ለማድረግ የተቀረፁ  የአጭር እና የረዥም ግዜ የፋይናንስ አማራጮችን ለክቡራን ደንበኞቹ አቅርቧል፡፡

ዋና ዋና  የብድር አገልግሎቶች፡

  • የጊዜ ገደብ ብድር (አጭር፣ መካከለኛ፣ ረዥም ጊዜ)
  • ኦቨርድራፍት ፋሲሊቲ
  • የወጪ ንግድ ቅድመ ጭነት ዱቤ ፋሲሊቲ
  • የመርቸንዳይዝ (ሸቀጣሸቀጥ) ብድር
  • የLC (Letter of credit) ፋሲሊቲ
  • የማህበር የፋይናንስንግ
  • የተያዙ ንብረቶችን በከፊል ፋይናንስ ማድረግ

የብድር እና ቅድመክፍያዎች ጥቅም

  • የሥራ ካፒታል እጥረትን ለመቅረፍ ያለመ ነዉ
  • በሁሉም የኢኮኖሚ ሴክተር ከዝቅተኛ ደረጃ እስከ ከፍተኛ ደረጃ እንደ ማኑፈክቸሪንግ፣ አግሮ-ፕሮሰሲንግ፣ ሆቴል፣ ግብርና፣ ግንባታ፣ ማዕድን፣ ወዘተ ፕሮጀክቶች ፋይናንስ ለማድረግ ያስችላል/ያመቻል፡፡
  • ዝቅተኛ እና መካከለኛ ደረጃ ፕሮጀክቶች/የንግድ ሥራዎች በዉጫዊ የኦኢባ ልማት ሸሪኮች የተክኒክ እና በከፊል ዋስትና ሽፋን ይደገፋሉ
  • ለአስቸኳይ የስራ የካፕታል ፍላጎትን ለማርካት ጊዜያዊ ብድርን በማመቻቸት ፍላጎቶን ያሟላል
  • አንዴ ህጋዊ እና የቁጥጥር ሰነዶችን መስፈርቶችን ካሟሉ አገልግሎት አሰጣጡ ብቁ እና ቀልጣፋ ነዉ
  • ሁሉም መስፈርቶች (ቼክ ሊስቶች) ጥያቄዎችን ባቀረቡ ጊዜ ከቅርንጫፋችን ይሰጦታል፡፡