ዲያስፖራ ፋይናንሲንግ

  • ዝቅተኛዉን እኩዪቲ(ቅድመ ክፍያ)፣ ብድር ሲመልሱ ፤ በዉጭ ምንዛሬ (ዶላር፣ዩሮ ወይም ፖዉንድ) መክፈል ለሚችሉ የዲያስፖራ ማህበረስብ እና ሌሎች ደንበኞች የመኖሪያ ቤት ግዥ ብድር፣ የተሽከርካሪ መግዣ ብድር እና ፔርሰናል ብድር እንሰጣለን፡፡
  • ዝቅተኛዉን እኩዪቲ(ቅድመ ክፍያ) 20% ከተበዳሪዎች የሚጠበቅ ሲሆን ቀሪዉን 80% ባንኩ ይሸፍናል፡፡ ገቢዎ እና ፍላጎትዎ ላይ ተመርኩዞ ብድሩ በ25 ዓመት ዉስጥ ተከፍሎ ያልቃል፡፡
  • ብድሩ በአነስተኛ የወለድ ምጣኔ የሚሰጥ ነዉ፡፡
  • የዲያስፖራዉ ማህበረሰብ ገቢያቸዉን የሚገልጽ ሰነድ፤ የጋብቻ ምስክር ወረቀት፣ የባለቤት(የባል/ሚስት) ግብር ከፋይ መታወቂያ((TIN)፣ ዬሎ ካርድና ሌሎች ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
  • ዲያስፖራዉ ዝቅተኛዉን እኩዪቲ(ቅድመ ክፍያ) እና የብድር ክፍያዉን በዉጭ ምንዛሬ (ዶላር፣ዩሮ ወይም ፖዉንድ) መክፈል እንደሚችል በጽሁፍ ካረጋገጠና ተጓዳኝ ሰነዶችን ካቀረበ ይህ አገልግሎት ለዲያስፖራዉ ቤተሰብ ሊሰጥ ይችላል፡፡
  • የብድሩ ጊዜ ሳይጠናቀቅ ተበዳሪዉ ቀድሞ ከፍሎ ከጨረሰ ሌላ ተጨማሪ ክፍያ( commitment fee) አይከፍልም፡፡
  • ከመኖሪያ ቤት ግዥ ፣ የተሽከርካሪ መግዣ እና ፔርሰናል ብድር ዉጭ የዲያሰፖራዉ የስራ ካፒታል ከፍ ብሎ የ20/80 ህጉን ተከትሎ የቢዝነስ እና ኢንቬስትመንት ብድር እንሰጣለን፡፡