የወኪል ባንኪንግ አገልግሎት

የወኪል ባንኪንግ ማለት የባንኩ ደንበኞች ባንኩ በወከላቸዉ ወኪሎች ዘንድ በመሄድ የተወሰነ የባንክ አገልግሎት የሚያገኙበት ነዉ፡፡የባንካችን የወኪል ባንክ አገልግሎት ብራንድ ስሙ ኦሮ-ኤጀንት ይባላል፡፡

በኦሮ-ኤጀንት አማካኝነት የሚሰጡ ዋና ዋና አገልግሎቶች፤

  • የሞባይል ዋሌት ሂሳብ መክፈት/መመዝገብ
  • ወደ ሞባይል ዋሌት እና ወደ መደበኛ ሂሳብ ገንዘብ ማስገባት
  • ከሞባይል ዋሌት ሂሳብ ገንዘብ ወጭ ማድረግ
  • ማስታወሻ፡- የሞባይል ዋሌት ማለት ስልክ ቁጥርዎን በመጠቀም ኤሌክትሮኒክ ገንዘብ የሚያጠራቅሙበት ሂሳብ ሲሆን ከላይ የተቀሱትን አገልገሎቶች የሚያገኙበት መንገድ ነዉ፡፡