የካርድ ባንኪንግ አገልግሎት

ኦ.ኢ.ባ የኤ.ቲ.ኤም ማሽኖቹን ለክቡራን ደንበኞቹ (ኦሮ ካርድ ወይም በረካ ካርድ ለያዙ) ለአጠቃቀም ምቹ በሆነ ስፍራ ተክሏል፡፡ማሽኖቻችን የማንኛዉንም ኤ.ቲ.ኤም ካርድ መቀበል ይችላሉ፡፡የባንካችን የካርድ ባንኪንግ አገልግሎት ብራንድ ስሙ ኦሮ-ካርድ ይባላል፡፡

ኤ.ቲ.ኤም ማሽኖቻችን በአራት ቋንቋዎች -አፋን ኦሮሞ፣ አማርኛ፣ ትግርኛ እና እንግሊዝኛ የ24 /7 አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡

እነዚህ አገልገሎቶች፤

  • ገንዘብ ወጭ ማድረግ
  • ያለዎትን ቀሪ ሂሳብ ማወቅ
  • አጭር የሂሳብ እንቅስቃሴ መግለጫ ማየት
  • ከሂሳብዎ ወደ ሌላ ሂሳብ ቁጥር ገንዘብ ማስተላለፍ