የባንኩ አመሰራረት
ከ
ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ /ኦ.ኢ.ባ/ አግባብነት ባላቸው ሕጐች፣ደንቦችና በ1952 የኢትዮጵያ የንግድ ሕግ እንዲሁም በገንዘብ ነክና ባንክ አዋጅ ቁጥር 83/1986 እና በባንክ ሥራ አዋጅ ቁጥር 592/2000 መሠረት በብር 1.5 ቢሊዮን የተፈቀደ ካፒታል ፣በብር 279.2 ሚሊዮን የተፈረመ ካፒታልና ብር 91.2 ሚሊዮን የተከፈለ ካፒታል ተመሥርቶ መስከረም 8 ቀን 2001 ዓ/ም ሕጋዊ የባንክ ንግድ ሥራ ፈቃድ አገኘ፡፡
ባንኩ የመጀመሪያ ቅርንጫፉን በደንበል የገበያ ማዕከል ሕንጻ ላይ ቦሌ ቅርንጫፍ በሚል ስያሜ ከፍቶ ጥቅምት 15 ቀን 2001 ዓ/ም በይፋ ሥራ ጀመረ፡፡ ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ የተፈረመ ካፒታሉን በእጥፍ ለማሳደግ የወሰነ ሲሆን የተከፈለ ካፒታሉም ብር 3 ቢሊዮን ደርሷል፡፡