የባንኩ ስኬቶች

 

ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል  ባንክ  ከተቋቋመበት  ጊዜ ጀምሮ በተለያዩ ምክንያቶች የፋይናንስ ተደራሽነት ለሌላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች የባንክ አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቷል። በዚህም ባንኩ የቅርንጫፎቹን ስርጭት ለማሳደግ ዋነኛ ትኩረት በማድረግ በሁሉም አካባቢ የባንክ አገልግሎት እንዲደረስ ከፍተኛ የመሪነት ሚና የተጫወተ ሲሆን በተለይ 26  ቅርንጫፎቹን  ስራ  በጀመረ  በስምንት  ወራት  ጊዜ  ዉስጥ ብቻ መክፈቱ እና በወቅቱ ከተከፈቱት ዉስጥ 80% የቅርንጫፎቹ ስርጭት ገጠሩን ያማከለ እንዲሆን ማድረጉ ፈር ቀዳጅ የግል ባንክ እንዲሆን አድርጐታል፡፡

ባንኩ ቦሌ መንገድ ኦሎምፒያ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ጌቱ  የንግድ  ማዕከል አጠገብ ያለውን ባለ 13 ፎቅ መንትያ  ህንጻ  በ210 ሚሊዮን ብር ወጪ የገዛ  ሲሆን፤  ባንኩ ዋና መስሪያ ቤቱንም በዚህ ለንግድ ምቹ በሆነው እና  መሠረተ  ልማቱ  በተሟላለት ህንጻ ላይ አድርጐ እየሰራ ይገኛል፡፡ ይህም ከሌሎች ባንኮች ባጭር ጊዜ ውስጥ የራሱ ዋና መሥሪያ ቤት ያለው ባንክ አድርጎታል፡፡

በአጠቃላይ ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ በተቋቋመ ጥቂት አመታት ውስጥ በህብረተሰቡ ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነትን እና መልካም ስምና ዝና በማትረፍ ተልኮውን በመወጣት ላይ የሚገኝ የህዝብ ባንክ ሆኗል፡፡