የቁጠባ ሂሳብ

የቁጠባ ሂሳብ ወለድ የሚታሰብበት የተቀማጭ ሂሳብ አገልገሎት ሲሆን ለማንኛዉም የህግ ሰዉነት ያለዉ ግለሰብ፣ ድርጅት ወይም ማህበር አገልግሎቱ ይሰጣል፡፡

የአገልግሎቱ መሠረታዊ ባህርያት

  • የቁጠባ ሂሳቡን ለመክፈት ዝቅተኛዉ የገንዘብ መጠን 50.00 ብር ነዉ፡፡ ሆኖም ግን አንድ ወር ብቻ የሚቆይ በዜሮ ሂሳብ መክፈት ይቻላል፡፡
  • በዜሮ ሂሳብ የተከፈተዉ የቁጠባ ሂሳብ በአንድ ወር ጊዜ ዉስጥ በትንሹ 50.00 ብር ተቀማጭ ካልተደረገ ሂሳቡ ይዘጋል፡፡
  • በህግ አካል ወይም በፍርድ ቤት የተረጋገጠ ህጋዊ ዉክልና ያለዉ ግለሰብ በዋናዉ ባለሂሳብ ስም ሂሳቡን ማንቀሳቀስ ይችላል፡፡
  • ከፍተኛ የገንዘብ መጠን ያለምንም ገደብ ማስቀመጥ ይቻላል፡፡
  • ግለሰቦች፣ ድርጅቶች፣ የፋይናንስ ተቋማት፣ማህበራት፣ክለቦች፣ ወዘተ ይህን ሂሳብ ከፍተዉ መጠቀም ይችላሉ፡፡
  • ሂሳቡን በጋራ (በእና ወይም እና/ወይም) ማንቀሳቀስ ይቻላል፡፡