ዓለም አቀፍ የሐዋላ አገልግሎት

የኦ.ኢ.ባን ፈጣን እና አስተማማኝ የሐዋላ አገልግሎቶችን በመጠቀም ከየትኛውም የዓለም ክፍል ለወዳጅ ዘመድ እና ለንግድ አጋሮች የተላከ ገንዘብ በቀላል እና ምቹ ሁኔታ ያገኛሉ፡፡

የባንካችን የሐዋላ አገልግሎት በሁለት ዋና ዋና ክፍሎች ይመደባል፡፡

ወደ ሀገር ውስጥ የሚገባ ሐዋላ (ገቢ ሐዋላ)

ይህ አገልግሎት ከዉጭ የተላከላቸዉን ገንዘብ በኔትዎርክ ከማንኛዉም የባንካችን ቅርንጫፎች የሚቀበሉበት ነዉ፡፡ይህም ከሚከተሉት መንገዶች በአንዱ ሊሆን ይችላል፡፡

  • በስዊፍት ኮዳችን (ORIRETAA) በኩል ከባንክ ወደ ባንክ ማስተላለፍ
  • በገንዘብ አስተላላፊ ድርጅቶች አማካኝነት

ኦኢባ ከሚከተሉት ታዋቂ አለም አቀፍ የገንዘብ አስተላላፊ ድርጅቶች ጋር በመስራት ፈጣንና ዘመናዊ አገልግሎት ይሰጣል፡፡

ዌስተርን ዩኒየን ፣ መኒ ግራም፣ ላሪ ኤክስቼንጅ፣ ሪያ ፋይናንሻል ሰርቪስ፣ደሀብሽል ትራንስፈር፣መኒ ኤክስቼንጅ፣ሽፍት ፋይናንሻል ሰርቪስ፣ጐልደን መኒ ትራንስፈር፣ትራንስ ፋስት፣ዩ ሬሚት፣ዎርልድ ሬሚት፣ኤክስኘረስ መኒ ትራንስፈር

ወደ ዉጭ ሀገር የሚላክ ሐዋላ(ወጪ ሐዋላ)

ይህ ዉጭ ሀገር ለሚኖሩ የኦ.ኢ.ባ ደንበኞች (ግለሰቦች ወይም ድርጅቶች) በጥያቄአቸዉ መሠረት የሚያገኙት የሐዋላ አገልግሎት  ይመለከታል፡፡

በባንኩ ደንበኞች ጥያቄ መሠረት ዉጭ ሀገር ለሚኖሩ  ግለሰቦች ወይም ድርጅቶች ክፍያዎች ሚላኩበት ሂደት ነዉ። ክፍያው ለማስመጣት አገልግሎት (≤ $ 5,000.00) ፣ የትምህርት  ክፍያዎች ፣ የአባልነት ክፍያዎች ፣ የማማከር ክፍያዎች ፣ የህክምና ሂሳቦች ፣ የሆቴል ቦታ ማስያዝ ፣ ኢንሹራንስ…ወዘተ ይፈጸማል፡፡