ኦኢባ እና የኦሮሚያ እርሻ እና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ ስምምነት ተፈራረሙ

ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ እና የኦሮሚያ እርሻ እና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ በጋራ ለመሥራት ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

የባንኩ ም/ፕሬዝዳንት አቶ ወልዴ ቡልቶ እና የኦሮሚያ እርሻ እና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ ም/ኃላፊ አቶ ጌቱ ገመቹ  የሁለቱም ተቋማት የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት ስምምነቱን ተፈራርመዋል፡፡

በስምምነቱ የግብርናዉን ክፍለ ኢኮኖሚ አቅም ከፍ ለማድረግ፣ለተዋናዮቹም የኢንተርፕሩነርሺፕ ልማት ስልጠናና የፋይናንስ አገልግሎት ለመስጠት የሚያግዝ ነዉ፡፡

ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ የግብርናዉን ዘርፍ ወደ ኢንዱስትሪ ለማሸጋገር በሚደረገዉ ርብርብ የራሱን ሚና ለመወጣት ከመቼዉም ጊዜ በበለጠ በቁርጠኝነት ይሠራል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.