ኦኢባ ለወጣት ስራፈጣሪዎች ስልጠና ሰጠ

ኦኢባ ለወጣት ስራፈጣሪዎች ስልጠና ሰጠ

ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ ለወጣት ስራ ፈጣሪዎች በኢንተርፐሩነርሺፕ ልማት ላይ የግማሽ ቀን ስልጠና መጋቢት 28 ቀን 2013 ዓ.ም በአዳማከ ተማ ሰጥቷል፡፡

ባንኩ መካከለኛውን የሕብረተሰብ ክፍል ማብቃት ተልዕኮዉ በመሆኑ ይህንኑ ለማሳካት መሰል ሥልጠናዎችን በመንደፍ ወጣት ሥራ ፈጣሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ዘርፈ ብዙ ሥራዎችን እየሠራ ይገኛል፡፡

የባንኩ ስትራቴጂ እና ለዉጥ ማኔጅመንት ም/ፕሬዝዳንት ኦቦ ጆቴ ቀናቴ እንደገለጹት ባንኩ ለአንድ ጊዜ ብቻ ስልጠና ሰጥቶ የሚያቆም ሣይሆን

ም/ፕሬዝዳንቱ አክለዉም ባንኩ ከሚመለከተዉ አካል ጋር በቅርበት በመሥራት ኢንተርፕራይዞችን ከፕሮግራሙ ጋር በማስተሳሰር የሚፈለገዉን ልማት ለማምጣት ተግቶ እንደሚሠራም ገልጸዋል፡፡

ከአዳማ ከተማ አስተዳደር ኢንተርፕራይዞች የተወጣጡ ሃምሳ የሚሆኑ ሥራ ፈጣሪ ወጣቶች የተሳተፉበት ሥልጠና በሶሰት ዋና ዋና አርዕስት፡- የኢንተርፕሩነርሺፕ ፅንሰ ሀሳብ፣ የቢዝነስ ሀሳብ ማመንጨት እና የቢዝነስ ዕቅድ አወጣጥ ላይ ያተኮረ ነበር::

Leave a Reply

Your email address will not be published.