እጃራ ፋይናንሲንግ

የኢጃራ ፋይናንሲንግ አገልግሎት /ኪራይ-ነክ ፋይናንሲንግ ( Leasing) ባንኩ ለኪራይ ሊውሉ የሚችሉ ንብረቶችን በደንበኛው ትዕዛዝ ወይም በራሱ ተነሳሽነት በመግዛት የሚያከራይ ሲሆን ባንኩ የሚያከራየውን ንብረት ቀድሞ በሚገባው ቃልኪዳን መሰረት የኪራይ ውሉ ሲያበቃ ወይም በመካከሉ ለተከራዩ በሸያጭ ወይም በስጦታ ሊያሰተላልፍ ይችላል፡፡ ደንበኛው እነዚህን ማሽነሪዎች (ተሽከርካሪዎች) በኪራይ ሲወስድ ከኪራይ ዋጋቸው በተጨማሪ ከንብረቱ ዋጋ የተወሰነውን እየከፈለ በመጨረሻም ንብረቱን የራሱ የሚያደርግበት አሰራር ፋይናንስግ ኢጃራ ይባላል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ ባንኩ የሚያከራየውን ንብረት የኪራይ ውሉ ሲያበቃ የንብረቱ ባለቤትነት ለተከራይ የማይተላለፍበትና ንብረቱ ወደ ባንኩ የሚመለስበት አሰራር ኦፕሬቲንግ ኢጃራኽ ይባላል፡፡

ኦፕሬቲንግ ኢጃራ

 • ሙሉ በሙሉ በሸሪዓው መርህ የተደገፈና ከወለድ የፀዳ የብድር/የፋይናንስግ አገልግሎት ነው፡
 • ባንኩ በግልጽ በተቀመጠ የኪራይ ጊዜ ያህል ንብረቱን ያከራያል፡፡
 • የኪራይ አከፋፈሉ በየወሩ (በውሉ በተገለጸው መሰረት) የሚከፈል ይሆናል፡፡
 • የሚከራውን ንብረት አጠቃቀም በውል ውስጥ በግልጽ ይቀመጣል፡፡
 • በኪራይ ወቅት የሚከሰቱ የንብረት ጉዳቶች በውሉ ውስጥ በግልጽና በማያሻማ ሁኔታ መቀመጥ አለበት ፡፡
 • ተከራይ በሥራ ወቅት ለሚከሰቱት ጥገናዎች እና ለንብረቱ ኃላፊነት ይወስዳል፡፡
 • ተከራይ በውሉ መሠረት ኪራዩን በወቅቱ ባይፈጽም ወይም ቢያዘገይ
 • ተደራራቢ ወለድ (compound interest) አይከፍልም፡፡ ነገር ግን ከፍተኛ ቅጣት ይኖረዋል፡፡
 • ንብረቱ /እቃው/ የተከራየበት የኪራይ ጊዜ ሲያበቃ የንበረቱ ባለቤትነት ለተከራይ አይተላለፍም፡፡
 • ለዚህ ፋይናንሲንግ አገልግሎት ባንኩ ማስያዣ ሊጠይቅ ይችላል፡፡

ፋይናንስግ ኢጃራ

 • ሙሉ በሙሉ በሸሪዓው መርህ የተደገፈና ከወለድ የፀዳ የብድር/ የፋይናንስግ አገልግሎት ነው፡፡
 • ባንኩ ኪራይና የንብረቱን ዋጋ ከደንበኛው በተቀመጠ ጊዜ ገደብ እያስከፈለ ባለቤትነቱን ያስተላልፋል፡፡
 • ባንኩ ዘላቂ ባለቤትነት በንብረቱ ላይ አይኖረውም፤ ኪራይን ጨምሮ ዕዳው እስኪጠናቀቅ የባለቤትነት ድርሻ ይኖረዋል፡፡
 • የንብረቱ ዋጋና ኪራይ አከፋፈል በየወሩ (በውሉ በተገለጸው መሰረት) የሚፈፀም ይሆናል፡፡
 • የንብረት አጠቃቀምና አስተዳደር በውል ውስጥ በግልጽ ይቀመጣል፡፡
 • ደንበኛው በሥራ ወቅት ለሚከሰቱት ጥገናዎች እና ለንብረቱ ኃላፊነት ይወስዳል፡፡
 • ደንበኛው በውሉ መሠረት ኪራዩን ባይፈጽም ወይም ቢያዘገይ ተደራራቢ ወለድ (compound interest) አይከፍልም፡፡ ነገር ግን ከፍተኛ ቅጣት ይኖረዋል፡፡
 • የግዢና ኪራይ ስምምነት የሚደረግበት ነው፡፡
 • ለዚህ ፋይናንሲንግ አገልግሎት ባንኩ ማስያዣ ሊጠይቅ ይችላል፡፡