እስትሲና ፋይናንሲንግ

የኢስቲስና ፋይናንሲንግ አገልግሎት

ተመርተው የተጠናቀቁ ዕቃዎችን ወይም ግንባታቸው የተጠናቀቁ ህንፃዎችን መግዛት የሚፈልጉ ደንበኞች በሚያቀርቡት ትዕዛዝ መሰረት ባንኩ በኢንዱስትሪ በማስመረት ወይም በህንፃ ግንባታ ስራ ዘርፍ ላይ በተሰማሩ ግለሰቦች (ድርጅቶች) በማስገንባት በእጅ በእጅ ወይም በዱቤ ሽያጭ የሚያስረክብበት የፋይናንሲንግ አገልግሎት ነው፡፡

የዚህ አይነት የፋይናንስ አገልግሎት ልዩ ባህሪያትና ጥቅሞቹ በጥቂቱ ፡

  • በውል ስምምነት ወቅት የሚደረግ ምንም ዓይነት የንብረት ርክክብ አይኖርም፡፡
  • ደንበኛውና ባንኩ ወደፊት ተሰርቶ ወይም ተመርቶ ወይም ተገንብቶ በሚቀርብ ጉዳይ ላይ ስምምነት የሚደርጉበት ነው፡፡
  • ባንኩ ከገዥዎች በተቀበለው ተዕዛዝ መነሻነት ከአምራቾች ወይም በህንፃ ግንባታ ስራ ዘርፍ ላይ ከተሰማሩ ግለሰቦች (ድርጅቶች)
  • ጋር የተለየ የሥራ ውል በመዋዋል ለድርጅቶቹ በጥሬ ገንዝብ ወይም በግብዓት ዓይነት ፋይናንስ ያቀርባል፡፡
  • የባንኩ ኢንጂነሮች (ማርኬቲንግ ባለሙያዎች) አስተያየት ከሰጡበት በኋላ በፍጥነት የሚፀድቅ ነው፡፡
  • ግልጽና ቀልጣፋ መረጃ የማጣራት ስራ የሚከናወንበት ነው፡፡
  • ለዚህ ፋይናንሲንግ አገልግሎት ባንኩ ማስያዣ ሊጠይቅ ይችላል፡፡