አማና ተንቀሳቃሽ ሂሳብ

አማና ተንቀሣቃሽ ሂሳብ

አማና ተንቀሳቃሽ የሂሳብ  አገልግሎት ማለት አስቀማጩ ደንበኛ ለገንዘቡ ደህንነት በባንኩ ዘንድ የሚያስቀምጥበት ባንኩም ዋስትና የሚሰጥበት ሲሆን ደንበኛው ገንዘቡን በሚፈልግበት ጊዜ በሙሉ ወይም በከፊል ማውጣት የሚችልበት አገልግሎት ነው፡፡

የዚህ አገልግሎት ልዩ ባህሪያትና ጥቅሞቹ ፡

  • አገልግሎቱ የሚሰጠው በቼክ ነው፡፡
  • ደንበኛው ገንዘቡን በሚፈልግበት ጊዜ ማስቀመጥም ሆነ ማውጣት ይችላል፡ ፡
  • ደንበኛው ገንዘቡን ያለገደብ (ያለውን በከፊል ወይም በሙሉ) ማውጣት ይችላል፡፡
  • በሁሉም ቅርንጫፎች አገልግሎቱን በኦንላይን (የኔትወርክ መረብ በመጠቀም) ማግኘት ይቻላል፡፡
  • በደንበኛው ጥያቄ መሰረት በወር አንድ ጊዜ የሂሳብ እንቅስቃሴ መግለጫ ይሰጣል፡፡
  • በዘርፉ የሰለጠኑ ባለሞያዎች በአገልግሎት መስጫ መስኮቶች ድጋፍና ምክር ያገኛሉ፡፡
  • ትርፍም ሆነ ኪሳራ ደንበኛው ላይ አያስከትልም፡፡
  • ዝቅተኛ የተቀማጭ ሂሳብ መጠን ብር 500 (አምስት መቶ ብር) ብቻ ነው፡፡