ተንቀሳቃሽ ሂሳብ

ተንቀሳቃሽ ሂሳብ  ወይም ቼኪንግ አካውንት ተብሎ የሚጠራና ማንበብና መጻፍ በሚችሉ ደንበኞች እና / ወይም በሕጋዊ ወኪላቸው የሚከፈት እና የሚሠራበት ሂሳብ ነው ፡፡ብዙውን ጊዜ ገንዘብ ወጪ የሚደረገዉ ባንኩ ለባለሂሳቡ በሚሰጠዉ ቼክ አማካኝነት ሲሆን አንዳንዴ ባለሂሳቡ በጽሐፍ በሚያቀርበዉ ትዕዛዝም የሚፈጸም ይሆናል ፡፡

የአገልግሎቱ መሠረታዊ ባህርያት

  • ይህን ሒሳብ ለመክፈት የሚያስፈልገው አነስተኛ የገንዘብ መጠን ለግለሰብ ብር 500 ሲሆን ለድርጅት ብር 1000 ነው ፡፡
  • በዋናው የባለሂሳቡ ስም በሕጋዊ ወኪል አማካኝነት ሊከፈት እና ሊንቀሳቀስ ይችላል ፡፡
  • በጋራ (እና ወይም እና / ወይም)ሊከፈት እና ሊንቀሳቀስ ይችላል፡፡