ሰላም ፋይናንሲንግ

የሰላም ፋይናንሲንግ አገልግሎት

በባንኩና በደንበኛው መካከል አስቀድመው በሚፈፀም ውል መሠረት በግብርና ስራ ላይ የተሰማሩ ግለሰቦች ወይም ድርጅቶች ምርታቸውን ሳይመረት ለባንኩ የሚሸጡበትና በጥሬ ገንዘብ የፋይናንስ አገልግሎት በማግኘት ወደፊት ከሚያመርተው ምርት በውሉ በተገለጸው ቦታ፣ጥራት፣መጠንና ጊዜ መሠረት በዓይነት/በምርት የሚመልሱበት የፋይናንስግ ዓይነት ነው፡፡

የዚህ አይነት የፋይናንስ አገልግሎት ልዩ ባህሪያትና ጥቅሞቹ በጥቂቱ፡

  • ደንበኛው ለባንኩ በቅድመ-ምርት በተስማሙበት ዋጋ የሚሸጥበትና
  • ለሥራ ማስኬጃ የሚሆነውን በጥሬ ገንዘብ ወድያው የሚያገኝበት ነው፡፡
  • ምርቱ ኢንሹራንስ ሽፋን (ተካፉል) ሊኖረው ይገባል፡፡
  • በቅድሚያ በተደረገው ውል ስምምነት መሠረት ደንበኛው ምርቱ ሲደርስ
  • ለባንኩ በዓይነት በተባለው ቦታ፣ጥራት፣መጠንና ጊዜ ያቀርባል፡፡ ይህም ለሁለቱም ወገኖች በግልፅ መታወቅ አለበት፡፡
  • ባንኩ በትይዩ ሰላም ምርቱን ለሶስተኛ ወገን ሊያስተላልፍ ወይንም በገበያ ዋጋ ሊሸጥ ይችላል፡፡
  • ለዚህ ፋይናንሲንግ አገልግሎት ባንኩ ማስያዣ ሊጠይቅ ይችላል፡፡