ራዕይ፣ ተልዕኮ እና እሴቶች

ራዕይ

የመጀመሪያ  ምርጫዎ  ባንክ  ሆኖ መገኘት

ተልዕኮ

አግባብነት ባላቸው ደንቦችና መመሪያዎች ማዕቀፍ ውስጥ የተሟላና የላቀ ጥራት ያለው የባንክ አገልግሎት መስጠት፣ቀጣይነት ላለው የንግድ ሥራ ትኩረት በመስጠት መካከለኛውን የሕብረተሰብ ክፍል ለማብቃትና ማህበራዊ ኃላፊነትን በብቃት ለመወጣት ብቃት ባለው በሰለጠነ እና በዲሲፒሊን በታነፀ የሰው ኃይል እንዲሁም ወቅቱ በሚጠይቀው የመረጃ ቴክኖሎጂ በመታገዝ የባለአክሲዮኖችን ትክክለኛ  እሴት ማሳደግና በህብረተሰቡ ዘንድ ተአማኒነትን ለማግኘት ተግተን እንሠራለን፡፡

እሴቶች

  • ለፅናት ለብርታትና ለጥብቅነት ዋጋ እንሰጣለን
  • ለደንበኞች እርካታ ዋጋ እንሰጣለን
  • ግልፅነትን፣ታማኝነትንና: ሚስጢረኝነትን እንደግፋለን
  • በቡድን መሥራትን እና ተተኪዎችን ለማዘጋጀት ተግተን እንሰራለን
  • ለመከባበር ዋጋ እንሰጣለን
  • ተወዳዳሪ፣የሥራ ፍላጐት ያለው፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ ዕውቀቱን የሚያሳድግና ተነሳሽነት ያለው የሰው ኃይል እናበረታታለን
  • የሚማርና አዲስ ነገር የሚፈጥር ድርጅት እናስፋፋለን
  • የየኔነት ስሜትን እናበረታታለን
  • ማህበራዊ ኃላፊነትን ለመወጣት ድርጅታዊ መርሆዎችን አጠንክረን እንቀጥላለን፡፡