ማህበራዊ ኃላፊነት

ኮርፖሬት ማህበራዊ ኃላፊነት ማለት በማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ እና አካባቢያዊ ሁኔታዎች ላይ አዎንታዊ ተፅእኖ የሚያሳርፍ ተግባር ሲሆን የተፈጥሮ ወይም  ሰዉ ሰራሽ አደጋዎች ሲያጋጥሙም  ምላሽ በመስጠት መንግስትም ሆነ ኅ/ሰቡ የሚወስዳቸዉ እርምጃዎችን ማገዝንም የሚያካትት ነው። ማህበራዊ ኃላፊነት ከኩባንያው የኮርፖሬት ራዕይ የሚመነጭ ነው፡፡

እነዚህን እውነታዎች በተገናዘበ መልኩ ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ ማህበራዊ ኃላፊነትን ከዋና ዋና ቢዝነስ ፕሮግራሞቹ ጋር አቀናጅቶ እየሠራ ይገኛል፡፡

ለአብነት ባለፉት አምስት ዓመታት ዉስጥ ለሀገር በቀል የበጎ አድራጎት ድርጅቶች፣ ለተለያዩ አደጋ ተጋላጭ የሆኑ የኅ/ሰብ ክፍሎች፣ ለመንግስት ፕሮጀክቶች እና ለሌሎችም በርካታ ችግሮች ምላሽ በመስጠት ኦ.አ.ባ  ወደ 50 ሚሊዮን የሚጠጋ ብር ለግሷል ፡፡

ከነዚህም መካከል፤

  • ኮቪድ -19ን ለመከላከል ለኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሶስት ሚሊዮን ብር ለግሷል፤
  • ኮቪድ -19ን ለመከላከል ለብሔራዊ ሀብት ማሰባሰብ ኮሚቴ አምስት ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርጓል፤
  • ለፊንፊኔ ከተማ አስተዳደር ለተማሪዎች ደብተር መግዣ ስድስት ሚሊዮን ብር ለግሷል ፤
  • ለሸገር አረንጓዴ ፕሮጀክት 10 ሚሊዮን ብር ሰጥቷል ፤
  • በድርቅ ለተጎዱ የማህበረሰብ ክፍሎች ከ 2.7 ሚሊዮን ብር በላይ ለግሷል፤
  • ለአካባቢ ጥበቃ ብር 400,000 (አራት መቶ ሺህ ብር) ሰጥቷል፤
  • በትምህርት ተደራሽነት ላይ ለሚሰሩ ሀገር በቀል በጎ አድራጎት ድርጅቶች ከ ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ለግሷል ፡፡
  • በተፈጥሮ እና በሰው ሰራሽ አደጋ ከቤት ንብረታቸዉ ለተፈናቀሉ ዜጎች ማቋቋሚያ የሚዉል 20 ሚሊዮን ብር አበርክቷል;
  • ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ አንድ ሚሊዮን ብር ሰጥቷል ፡፡