ሙዳራባ ፋይናንሲንግ

የሙራባኻ ፋይናንሲንግ አገልግሎት ባንኩ በራሱ ተነሳሽነት ወይም በደንበኛው ትዕዛዝ በሸሪዓ መርህ የተፈቀዱ የፍጆታ ዕቃዎችን፣ ማሽነሪዎችን ወይም ከባድ ተሽከርካሪዎችን በመግዛትና በግዥ ወቅት የወጡ ልዮ ልዩ ወጪዎችንና የባንኩን ትርፍ መጠን በእቃው ዋጋ ላይ በመጨመር የፋይናንስ አገልግሎት ለሚጠይቁ ደንበኞች በሽያጭ የሚያስተላልፍበት የባንክ አሰራር ነው፡፡ነገር ግን ብዙ ጊዜ ይህ አገልግሎት የሚፈፀመው በደንበኛውና በባንኩ መካከል አስቀድመው በሚደረግ የስምምነት ውል መሠረት ነው፡፡ ባንኩ ዕቃዎችን ለደንበኛው በውሉ መሰረት እስኪያስተላልፍ ድረስ የባለቤትነት መብት ይኖረዋል፡፡

የሙራባኻ ፋይናንሲንግ አገልግሎት የሚያገኙ ደንበኞች ማንኛውም ፡-

 • በአስመጭነት ሥራ የተሰማራ፤
 • በሀገር ውስጥ በጅምላም ሆነ በችርቻሮ ንግድ የተሰማራ፣የግንባታ ሥራ ላይ የተሠማራና የግንባታ ግብዓቶችን (ከባድ በትራንስፖርት አገልግሎት አቅራቢነት ላይ የተሰማራ፤
 • ተሽከርካሪዎችን ለራሱ በመግዛት ወይም ገዝቶ በማከራየት ሥራ የተሠማራ፤
 • የኢንዱስትሪ ምርት አምርቶ በመሸጥ ሥራ የተሠማራ ለኢንዱስትሪ ምርቱ ግብዓቶች ለመግዛት የሚፈልግ አገልግሎቱን መጠቀም ይችላል፡፡

የዚህ ፋይናንሲንግ አገልግሎት ልዩ ባህሪያትና ጥቅሞቹ በጥቂቱ ፡

 • ሙሉ በሙሉ በሸሪዓው መርህ የተደገፈና ከወለድ የፀዳ የብድር/የፋይናንስግ አገልግሎት ነው፡፡
 • ባንኩ የትርፍ መጠኑን በእቃ ዋጋ ላይ በመጨመር ለደንበኛው የሚያስተላልፍበት ስርዓት ነው፡፡
 • ባንኩ የዕቃውን ባለቤትነት በራሱ ካደረገ በኋላ ለደንበኛው ያስተላልፋል፤
 • ባንኩ የሚሸጠውን እቃ ራሱ ሊገዛ ወይም በወኪል ሊያስገዛ ይችላል፡፡ ተበዳሪው ደንበኛ ሊወከል ይችላል፡፡
 • ደንበኛው የዕቃውን ዋጋ ወድያው እጅ በእጅ ወይም ቀስ በቀስ በዱቤ ክፍያ ሊፈፅም ይችላል፡፡
 • ለአጭርና መካከለኛ ጊዜ የፋይናንስ ፍላጎት የሚውል አሰራር ነው፡፡
 • ለዚህ የፋይናንሲንግ አገልግሎት ባንኩ ማስያዣ ሊጠይቅ ይችላል፡፡