ሙዳረባ የኢንቨስትመንት ሂሳብ

እነዚህ ሂሳቦች ደንበኛውና ባንኩ በኢንቨስትመንት ላይ እንዲሰማሩ እድል የሚሰጥና ትርፍ የሚያስገኙ ናቸው፡፡ ትርፉ እንደ ስምምነታቸው ሲሆን ኪሳራ ቢደርስ እንደ ገንዘብ መዋጮአቸው ሆኖ የሸሪዓ ኦዲት ማረጋገጫ ሲሰጥ ብቻ ይተገበራል፡፡ ይህ አሰራር በሁለት ይከፈላል፡፡

የተገደበ የኢንቨስትመንት ሒሳብ ቋት

ደንበኛው የኢንቨስትመንት ሴክተሩን የሚወስንበት የሂሳብ ዓይነት ሲሆን ባንኩ ደንበኛው በፈቀዳቸው ሀላል የስራ ዘርፎች ላይ ብቻ ሊያውል ይገደዳል፡፡

የዚህ ዓይነት የኢንቨስትመንት ሒሳብ ቋት ልዩ ባህሪያትና ጥቅሞቹ በጥቂቱ፡

  • ከወለድ ነጻ የሆነና ጠቀም ያለ ትርፍ የሚያስገኝ ነው፡፡
  • ትርፍ ክፍፍሉ በባንኩና በደንበኛው መካከል አስቀድመው በተደረሰው::
  • ስምምነት ሲሆን ኪሳራ ቢያጋጥም በኢንቨስትመንት ድርሻ መጠን በሸሪዓ ኦዲት ማረጋገጫ መሠረት ገንዘብ አስቀማጩ ላይም ይኖራል፡፡
  • የትርፍ ክፍፍሉና ክፍያ እንደስምምነት ሆኖ የኢንቨስትመንት ጊዜን ማዕከል በማድረግ በየሩብ ዓመት፤ በመንፈቅ ዓመት ወይም በዓመት ይከናወናል፡፡
  • ዝቅተኛ የተቀማጭ ሂሳብ መጠን ብር 10,000,000 (አስር ሚሊዮን ብር) ነው፡፡
  • ለዚህ አገልግሎት ባንኩ በጊዜ የተገደበ ሰርተፊኬት ይሰጣል፡፡

ያልተገደበ የኢንቨስትመንት ሒሳብ ቋት

ያልተገደበ የሙዳራባ ኢንቨስትመንት አካውንት/ፈንድ/ ማለት ፈንዱ የሚውልበትን የቢዝነስ/የንግድ ዓይነት ባንኩ የፈንዱን ባለቤት ፍላጎትና ፍቃድ መጠየቅ bሳያስፈልገው ባንኩ አዋጭ በሆኑ የንግድ ዘርፎች ላይ የሚያውልበት ነው፡፡

የዚህ ዓይነት የኢንቨስትመንት ሒሳብ ቋት ልዩ ባህሪያትና ጥቅሞቹ በጥቂቱ፡

  • ከወለድ ነጻ የሆነና ጠቀም ያለ ትርፍ የሚያስገኝ ነው፡፡
  • ትርፍና ኪሳራ ባንኩና ደንበኛው ባዋጡትና በተስማሙት መሰረት ይሆናል፡ ፡
  • የትርፍ ክፍፍሉና ክፍያ እንደስምምነት ሆኖ የኢንቨስትመንት ዝቅተኛ የተቀማጭ ሂሳብ መጠን ብር 1,000,000 (አንድ ሚሊየን ብር) ነው፡፡
  • ለዚህ አገልግሎት ባንኩ በጊዜ የተገደበ ሰርተፊኬት ይሰጣል፡፡