ኦሮሚያ ባንክ በሁሉም የአፈፃፀም መመዘኛዎች የዕድገት ጎዳና ላይ እየተጓዘ ይገኛል፡፡
ባንካችን 12ኛውን የባለ አክሲዮኖች ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባዔን ቅዳሜ ታህሳስ 16 ቀን 2014 ዓ.ም ያካሄደ ሲሆን በቀረበዉ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሪፖርት ላይ እድገቱ ቀርቧል፡፡
በዚህም መሠረት የባንካችን ጠቅላላ ሀብት በ23% ጨምሮ ብር 41.7 ቢልዮን ደርሷል፤ በተጨማሪም የባንካችን የደንበኞች ብዛት ከቀዳሚው ዓመት ጋር ሲነጻጸር በ45 ከመቶ በመጨመር 2.49 ሚሊዮን የደረሰ ሲሆን፣ የባንኩ ተቀማጭ ገንዘብ በ24 ከመቶ በመጨመር 34.35 ቢልዮን ደርሷል፡፡
ባንካችን በመደበኛው የባንክ ሥራ የሰጠው ብድር እና ከወለድ ነፃ በሆነው የባንክ ሥራ የሰጠው ፋይናንሲንግ በድምር ከቀዳሚው ዓመት በ27 ከመቶ አድጎ ብር 25.77 ቢልዮን ደርሷል፡፡ከዚሁ አፈጻጸም ጋር ተያይዞ ባንካችን በበጀት ዓመቱ ከግብር በፊት ብር 1.13 ቢሊዮን ትርፍ አስመዝግᎆል፡፡
በሌላ በኩል የባንካችንን ሁለንተናዊ አፈጻፀምና የመፈጸም አቅም በወሳኝ ሁኔታ እንደሚያሻግር የታመነበት የላቀ የደንበኛ አገልገሎት አሰጣጣችንን በእጅጉ የሚያሳልጥ የሦስተኛ ዘመን የአምስት አመት የስትራቴጂ ዕቅድ ተቀርጾ የትግበራ ጅማሮ ላይ ይገኛል። አዲሱ ብራንዳችንም በአዲስ ገጽታ፤ በአዲስ ምልከታና በታደሰ አስተሳሰብ ደንበኞቻችንን የምናገለግልበት የቃልኪዳን ምልክታችን ነዉ፡፡
ለስኬትዎ እንተጋለን!
