ለቤይክ ዋዲዓ የቁጠባ ሂሳብ

ለቤይክ-ወዲዓ የቁጠባ ሂሳብ አገልግሎት

ይህ ልዩ የቁጠባ የሂሳብ አገልግሎት የሀጂ እና ኡምራ ጉዞ ማድረግ ለሚፈልጉ ደንበኞቻችን አማራጭ የሚሰጥ ሲሆን በቅድሚያ በመቆጠብ ለጉዞ የሚያስፈልገውን ገንዘብ የሚያጠራቅሙበት የቁጠባ አገልግሎት ነው፡፡

ልዩ ባህሪያትና ጥቅሞቹ

  • ሐጅና ዑምራ ለማድረግ ለሚፈልጉ (ኒያ ላደረጉ) ደንበኞች ዕቅዳቸውን በቀላሉ የሚያሳኩበት ልዩ የቁጠባ ሂሳብ ነው፡፡ ሙስሊም ደንበኞቻችን የሃጂና ኡም ራ ጉዞን በቀላሉ እንዲያከናውኑ ይ ረዳል፡፡
  • የሃይማኖታዊ ጉዞውን ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ጋር በመተባበር ቁጠባውን በብር በመቀበል በጉዞ ወቅት የሚያስፈልገውን የውጪ ምንዛሪ ደግሞ በዕቅድ ይዘን እንድናቀርብ ይረዳናል፡፡
  • ዝቅተኛ (መነሻ) የቁጠባ መጠን የለውም፤ ደንበኛው አቅሙ የፈቀደውን የገንዘብ መጠን ያህል በሚመቸው ሁኔታ መቆጠብ ይችላል፡፡
  • ደንበኛው ገንዘቡን በፈለገ ጊዜ ማውጣት ይችላል፡፡
  • ይህ አገልግሎት በልዩ የቁጠባ ደብተር የሚንቀሳቀስ ይሆናል፡፡
  • የአስቀማጭ ዕድሜ ገደብ የለውም፤ ከ18 ዓመት በታች ለሆኑ ልጆች ወላጅ/አሳዳጊ ስለልጁ መክፈት ይችላል፡፡
  • ሂሳቡን ለመክፈት ምንም ዓይነት ክፍያ የለውም፤ ከ50 ብር ጀምሮ ለሐ ጅ/ ዑምራ ከሚያስፈልገውም በላይ ማ ስቀመጥ ይችላል፤ በየዓመቱ የሚሄዱት ሐጃጆች ጭምር፡፡