ሀንዱራ – ልዩ የልጆች የዋዲዓ ቁጠባ ሂሳብ

ይህ ልዩ የዋዲዓ ሂሳብ ወላጆች ወይም አሳዳጊዎች ከ18 ዓመት በታች ለሆኑ ልጆቻቸዉ የሚከፍቱት ሲሆን ልጆች ለወደፊት ትምህርታቸዉም ይሁን ኑሮአቸዉን የሚመሩበት ልዩ ጥቅም የሚያስገኝ ነዉ፡፡ሂሳቡን በህፃኑ ወላጆች/አሳዳጊዎች በጋራ ወይም በተናጠል ሊከፍቱ ይችላሉ፡፡ ሲከፍቱም ያለምንም ክፍያ ሊሆን የሚችል ሲሆን በአንድ ወር ጊዜ ዉስጥ ቁጠባ መጀመር አለበት፡፡ የህፃኑ ስም ከወላጆች/አሳዳጊዎች ስም ቀጥሎ መጻፍ አለበት፡፡በማንኛዉም ጊዜ የፈለጉትን መጠን ገንዘብ ማዉጣት ይችላሉ። ልጁ 18 ዓመት ሲሞላዉ ሂሳቡ ሙሉ በመሉ በስሙ የሚዞር ሲሆን ወደ መደበኛ የቁጠባ ሂሳብ ይቀየራል። ይህ አገልግሎት የሼሪዓ ህግን ተከትሎ የሚሰጥ ነው፡፡

  • ይህ የቁጠባ ሂሳብ በወላጆቻቸዉ እንክብካቤ ሥር ላሉ ከ18 ዓመት በታች ለሆኑ ሕፃናት የሚሰጥ ነዉ፤
  • ሂሳቡን የህፃኑ ወላጆች/አሳዳጊዎች በጋራ ወይም በተናጠል ሊከፍቱ ይችላሉ።
  • የህፃኑ ስም ከወላጆች/አሳዳጊዎች ስም ቀጥሎ መጻፍ አለበት።
  • ይህ የቁጠባ ሂሳብ ሕፃኑ ዕድሜዉ እስኪደርስ የሚንቀሳቀሰዉ በወላጆች ወይም አሳዳጊዎች ነዉ፤
  • ልጁ ሂሳቡን ለማንቀሳቀስ ዕድሜ ላይ እስኪደርስ በቁጠባ ደብተር ይንቀሳቀሳል፤
  • ለዚህ ቁጠባ ሂሳብ ማንኛዉም የክፍያ ካርድ አይሰራለትም፤
  • ሂሳቡ ሲከፈት ያለምንም ክፍያ ሊሆን የሚችል ሲሆን በአንድ ወር ጊዜ ዉስጥ ቁጠባ መጀመር አለበት፡፡
  • በማንኛዉም ጊዜ የፈለጉትን መጠን ገንዘብ ማዉጣት ይችላሉ።
  • ባለሂሳቡ ልጅ 18 ዓመት ሲሞላዉ ክፍያ መቀበል ይችላል፤ ሂሳቡም ወደ መደበኛ የቁጠባ ሂሳብ ይቀየራል።
  • ከ18 ዓመት በኃላ ልጁ ያለ ወላጆች/አሳዳጊዎች እርዳታ ሂሳቡን የማንቀሳቀስ መብት አለዉ፡፡